እንኳን ወደ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ደ/ወ/ቅ/ማርያም ድህረ ገፅ በሰላም መጡ።

In the name of the Father, the Son and the Holy Sprit, one God; the Church welcomes you to the website of St. Mary of Debrework of the Ethiopian orthodox church. The main objective of the website is to give you an insight and general information about Ethiopian orthodox church in Ireland which was established in June 28, 2008 by His Grace Abune Entons, Archbishop of Ethiopian Orthodox in Northern and North Eastern Europe. Your comment, participation and feedback are most welcome. God bless the holy land Ethiopia. Amen

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ቅድስት ቤተክርስቲያን እንኳን ወደ ደብረወርቅ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ድረ -ገፅ እንኳን ደሕና መጡ እንላለን። የዚሕ ድረ-ገፅ ዋና አላማ በአየርላንድ አገር በደብሊን ከተማ የምትገኘውን በ ሰኔ ፳፩ ቀን ፪ሺህ ዓ.ም በብጹዕ አቡነ እንጦንስ የሰሜንና የምዕራብ አውሮፓ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተባርካ የተከፈተችውን ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ ማስቃኘት ነው። በድረ - ገፅ ላይ የበኩልዎትን ተሳትፎ፣አስተዋፅኦ እና አስተያየት እንዲያበረክቱም ቅድስት ቤተክርስቲያችን ትጋብዛለች። እግዚአብሔር ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ይባርክ ። አሜን!!

ሰኔ 21 የሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብሊን ደብረ ወርቅ ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተከበረው እሁድ ሰኔ 26 2008 ዓ ም/june 3 2016/ ነበር። የዚህን ዓመት ዓመታዊ ክብረ በዓላት ልዩ የሚያደርገው ቤተ ክርስቲያ ከተመሰረተች 6ኛ ዓመት መሆኑና ይህ በዓል በሚከበርበት ጊዜ በለንደን ከሚገኙ ካህናትና ምእመናን በቁጥር ከፍ ያሉ ምእመናን መገኘታቸው ነበር ።በበዓሉ ከተገኙት ካህናት መካከል መልአከ ሰላም ቀሲስ አዲስ ገብረ ኪዳን ሊቀ ጉባዔ ቀሲስ ጥበበ ሲሆኑ በለንደን ደብረ መድኃኒት ቅድስት ሥላሴ በአገልግሎት የሚገኙ ሁለት ዲያቆናት ዲ/ን ፈለቀ እና ዲ/ን ካሌብ በመገኘት አገልግልት የሰጡ ሲሆን በዲያቆናቱ አስተባባሪነት ቁጥራቸው ከ15 የሚበልጡ የሰንበት ት/ቤት አባላትና ምዕመናን በደብሩ ከሚገኙ የሰንበት ት/ቤት አባላትና ምእምናን ጋር በመሆን ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ከዋዜማው ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል። ይህን መሰሉ በዓል ከከተማው ውጪ ከተገኙ ምእመናን ጋር ሲከብር የመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በደብሩ ምእመናንና በእንግዶቹ መካከል የተፈጠረው የአግልግሎት መግባባት በዓሉን በየዓመቱ በደብሩ በመገኘት ለማክበር ልዩ መግባባት ላይ እንዲደረስ አስችሏል ከዋዜማው ጀምሮ የተካሄደው መርሐ ግብር በሰንበት ት/ት ቤት አባላት ዝማሬና የተለያዩ ሥነ ጽሁፎች የቀረብ ሲሆን በእንግድነት በተገኙ ካህናት ስብከተ ወንጔልና ምክር ለምእመናኑ በሰፊው ተሰቶአል። ከክብረ በዓሉም በኋላ በተደረገ ልዩ መርሓግብር የገቢማሰባሰቢያ የተከናወነ ሲሆን ከለንደን ከመጡ እንግዶጭ 700 ዩሮ በላይ ድጋፍ ተደርጓል ከዚህው ጋር በተያያዘ በበዓል አዘጋጅ ኮሚቴ የቀረቡ ጨረታ እና ለሺያጭ የረቡ ስእላ ማርያም መስቀል ሌሎጭም ለምእመናኑ በመቅረብ ቤተ ክርስቲያኗን በገቢ ያገዘ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ምህረት ቀሲስ አንተነህ ጌጡ አማካኝነት በዓሉን ለማክበር ለተገኙ እንግዶ እና ምእመናን ምስጋና ከቀረበ በኋላ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ሐዲስ አማካኝነት ምክርና የመዝጊያ ጸሎት በማድረግ የዕሉቱ መርሐ ግብር ፍጻሜ ሆኖአል
ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ ዝምድና አለው፡፡ ይልቁንም በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ ነበረው፡
በኢትዬዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ደብረ ወርቅ ቅድስተ ማርያም ደብሊን ሕፃናት መዘምራን ........
PLEASE DONATE OUR CHURCH TODAY
GOD BLESS YOU
&