News / ዜና

 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
 “ወሰላም በምድር – በምድር ሰላም”  

አሜን።

ሰኔ 21 የተከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

 

ሰኔ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ትናንት ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ወረደ:: ፊልዽስዩስ በምትባል ሃገር በዼጥሮስ እጅ የመጀመሪያዋን ቤተ_ክርስቲያን አነጸ ብለን ነበር:: በዚህች ዕለት ደግሞ አእላፍ መላዕክትን: ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዟት ወረደ:: ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ:-

1.አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ

ሥርዓተ ቤተ ክርረስቲያንን አሳየ::

2.ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ_ዼጥሮስን ከመካከል አቁሞ “አርሳይሮስ” ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት “አክዮስ” እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ “ይደልዎ”: በዐማርኛው ደግሞ “ይገባዋል: ያሥምርለት” እንደ ማለት ነው::

ጌታችን ይሕን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ:: አማናዊት ማሕደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ: ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ: ቅዱስ_እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ: ሐዋርያት ድንግልን ከበው: መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቁመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ:: በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው:: ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን እነጹ:: ይህችን ዕለትየሚያከብራትን አከብረዋለሁ:: ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋር ዐረገ::

ሰኔ_ጐልጐታ

ዳግመኛ በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ይታሰባል::

ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮ

እኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ:: ቅዱስ ቶማስም ያመኑትን “ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሸሹ” ብሎ መከራቸው:: ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደ መሸታ ቤት ይገባል:: ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለ መሸተኛዋ ሴት እንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው “እንዴት ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?” በሚል ሰይፍ አውጥቶ አንገቷን ቆረጣት:: እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል:: የሠራው ሥራ (መግደሉ) ግን አሕዛባዊ ግብር ነው:: በማግስቱ ቅዱስ ቶማስ ነገሩን ሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና “ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመ ማነው?” ሲል ጠየቀ:: ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚል ዝም አለ:: ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና “ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ” አለ:: ሰውየው ተራውን ጠብቆ ሊያነሳ ሲል እጁ ሰለለች:: ሐዋርያው “ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?” አለው:: እሱም እንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ:: ቅዱስ ቶማስ ግን ሕዝቡ ሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ “አስከሬኑን አምጡልኝ” አለ:: የወጣቱን እጅ ፈውሶ “በል . . የገደልኩሽ እኔ: የሚያስነሳሽ ግን ጌታየ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው . . . ብለህ አንገቷን ቀጥለው” አለው:: እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች:: ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል::

ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን::

 

ሰኔ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

 

1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

 

2.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን

 

3.ቅዱሳን ሐዋርያት

 

4.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት

 

5.ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ

 

6.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ

 

7.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ

 

8.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር (ሰማዕት)

 

9.አባ ከላድያኖስ ሊቀ ዻዻሳት

 

ወርኃዊ በዓላት

 

1፡ አበው ጎርጎርዮሳት

 

2፡ አባ ምዕመነ ድንግል

 

3፡ አባ ዓምደ ሥላሴ

 

4፡ አባ አሮን ሶርያዊ

 

5፡ አባ መርትያኖስ

 

6፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል

 

ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . . አሕዛብም ጽድቅሽን: ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ:: የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ:: በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: +”+ (ኢሳ. 62:1-3)

20160703_124927 20160703_124930 20160703_133700 20160703_120749 20160703_120919

በሰኔ 20 ለመዠመሪያ ጊዜ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በፊልጵስዩስ የተሠራችው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ትታሰባለች፤ ይኸውም የቤተ ክርስቲያን ታሪክና መጽሐፈ ስንክሳርእንደሚያስረዳን ጳውሎስና በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ከተማ ገብተው ባስተማሩ ጊዜ ሕዝቡ “መካነ ጸሎት ለዩልን” ብለዋቸዋል፤ ይኽነንም ለጴጥሮስ ላኩበት፤ ከዚያም ወደ ሱባዔ ገቡ፤ሱባዔውም ሲፈጸም ጌታ ሐዋርያትን የሞቱትን አስነሥቶ ያሉትን ጠርቶ በሕይወተ ሥጋ በፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፤ “በናቴ ስም አብያተ ክርስቲያናት ሊታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንፃ ቤተክርስቲያንን ላሳያችኊ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናትን ላስተምራችኊ ሰብስቤያችኋለኊ” ብሏቸው፤ ወደ ምሥራቅ አገር ይዟቸው ወጣ፤ በዚያ በምሥራቅ ሀገር ሦስት ደንጊያዎች ነበሩ ተራርቀውየነበሩትን አቀራረባቸው፤ ጥቃቅን የነበሩትን ታላላቅ አደረጋቸው፤ ቁመቱን ወርዱን ለክቶ ሰጣቸው፤ ቁመቱ 24 ወርዱ 12 ክንድ ነው፡፡

24 24 ካህናተ ሰማይ አምሳል ነው፤ 12 12 ሐዋርያት አምሳል፤ ከዚኽ በኋላ ሥራ ዠመሩ፤ ሲሠሩትም ሰም እሳት ሲያሳዩት እንዲለመልም በእጃቸው ላይ እየተሳበ ሠርተውፈጽመውታል፤ ይኽ የኾነ እመቤታችን ባረገች በአራተኛው ዓመት በሰኔ 20 ቀን ነው፤ 21ኛው ቀን ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ መጣ፤ እመቤታችንን ታቦት፤ ሐዋያትን ልኡካን አድርጎ፤ጌታ ዐቢይ ካህን ኾኖ ቀድሶ አቊርቧቸዋል፤ ከዚያም “እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ” (ከእንግዲኽ ወዲኽ እናንተ እንዲኽ ሥሩብሎ አዝዟቸው ዐርጓል፤ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንየተዠመረ በቅድስት ድንግል ስም ነው፡፡

ሦስቱ ደንጊያዎች የሥላሴ አምሳል ናቸው፤ ከታች አቀማመጣቸው 3 ከላይ ሕንፃቸው 1 ነው ይኽም የአንድነታቸው የሦስትነተኛው አምሳል ነው፤ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያምዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፡- 
በሠላስ አእባን ገጸ ሥላሴሁ ለአምሮ
ሐኒጸ ቤትኪ ድንግል ድኅረ ፈጸመ ሣርሮ
አመ ወረደ ለበዓል ምስሌኪ በአማኅብሮ
እንዘ ይብላ ቃለ ለዘምሮ
ልዑል ቀደሰ ማኅደሮ
ደናግል ለጽጌኪ ዘበጣ ከበሮ
(
ድንግል በአካል ሦስት መኾኑን ለመግለጽ በሦስት ድንጋዮች ቤትሽን መሥራት ከፈጸመ በኋላ፤ ከአንቺ ጋር ለበዓል በተገለጸ ጊዜ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ እያሉ ልጅሽን ለማመስገን ደናግልበከበሮ ምስጋናን አቀረቡበማለት ገልጸዋል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯ በሰማያት አምሳል እንደኾነ ሊቃውንት ይተነትናሉ፤ ይኸውም የመዠመሪያዋ ሰማይ “ጽርሐ አርያም” ስትባል ከእሳት ብርሃኗን ነሥቶ ከብርሃን ብርሃንንጠምቆ አጥርቶ፤ ኹለንተናዋን በብርሃን ቀለም ሸልሟታል “አልቦ ሰማይ ዘይጼልል ላዕሌሃ እስመ መልዕልታዊት ወጽንፋዊት ይእቲ ወኲለንታሃ ብርሃን ፍጹም ዘኢይትነገር በልሳነ ኲሉፍጡር ወኲሎሙ ብርሃናት አምሳለ ቀለምጺጸ እሳት በኀቤሃ” ይላል  ብርሃኗን ማንም ከቶ ሊገልጸው አይችልም፤ ከርሷ ብርሃን አንጻር ሲታዩ ሌሎቹ ብርሃናት የእሳት ፍንጣሪ ያኽላሉ፤ከሰማይ ኹሉ በላይ ስትኾን ከርሷ በላይ ምንም ሰማይ የለም፤ ከዚኽ የተነሣ “ሰማየ ሰማያት” ትባላለች (ዘዳ ፲፥፲፬፤ ፩ነገ ፰፥፳፯)፡፡

ምሳሌነቷን ሊቃውንት በመጽሐፈ ቅዳሴ መቅድም ላይ የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ስለመሠራቱ ሲተነተን በጽርሐ አርያም ውስጥ መንበረ ብርሃን፣ ታቦተ ብርሃን፣ መንጦላዕተ ብርሃን፣አራቱ ጸወርተ መንበር፣ ኻያ አራቱ ዐጠንተ መንበር ይኖራሉ፤ ጽርሐ አርያም የመቅደስ፤ መንበረ ብርሃን የመንበር፤ ታቦተ ብርሃን የታቦት፤ መንጦላዕተ ብርሃን የመንጦላዕት፤ አራቱጸወርተ መንበር የአራቱ ሊቃነ ጳጳሳት፤ ፳፬ቱ ዐጠንተ መንበር የጳጳሳት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል ናቸው፡፡

ዳግመኛም ኢዮር፣ ራማ፣ ኤረር በተባሉ በሦስቱ ሰማያት አምሳል ቤተ ክርስቲያን ሦስት ክፍል ኾና ማለት መቅደስ፣ ቅድስት፣ ቅኔ ማሕሌት ኾና ታንጻለች፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫበመጽሐፈ ሰዓታቱ ላይም “ወኊልቈሙ ለእሙንቱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት መናብርት ወሥልጣናት አጋእዝት ወኀይላት ወሊቃናት ኪሩቤል ወሱራፌል ይጸርሁ ወይብሉ ይትባረክእግዚአብሔር አምላከ እስራኤል ወቡርክት ዛቲ ቤተ ክርስቲያን እንተ አሕዛብ ትመስል ኀይለ ሰማያት” (የእነዚኽ መላእክት የመላእክት አለቆች ቊጥርም መናብርትና ሥልጣናት፣አጋዕዝትና ኀይላት፣ ሊቃናት፣ ኪሩቤልና ሱራፌል ነው፤ እየጮኹም እንዲኽ ይላሉ የእስራኤል አምላክ ይመስገን የሕዝቡ የአሕዛቡ የምትኾን የተባረከች ቤተ ክርስቲያን የሰማያት ኀይልንትመስላለችይላል፡፡

ሊቁ ሰራዊተ መላእክትን በሚያመሰግንበት በዚኽ ክፍል ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯና እና አከፋፈሏ በመላእክት ከተማ እና በአሰፋፈራቸው ልክ የተመሰለች መኾኗን አስረግጦአስተምሯል፡ይኸውም ሦስቱ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች (መቅደስ፣ ቅድስት፣ ቅኔ ማሕሌትየሦስቱ ዓለመ መላእክት ምሳሌ ሲኾን ይኸውም መቅደስ የኢዮር፤ ቅድስት የራማ፤ ቅኔማሕሌት የኤረር ምሳሌ ናቸው፡፡

ኢዮር በተባለችው ሰማይ ኪሩቤል፣ ሱራፌል፣ ኀይላት ይኖራሉ፡፡ ራማ በተባለችው ሰማይ አርባብ፣ መናብርት፣ ሥልጣናት ይኖራሉ፡፡ ኤረር በተባለችው ሰማይ ሊቃናት፣ መኳንንት፣ መላእክትይኖራሉ፡፡ እነዚኽ ፱ኙ ነገድ የ፱ኙ መዓርጋተ ቤተ ክርስቲያን አምሳል ናቸው፡፡ ይኸውም በኢዮር የሚኖሩት ኪሩቤል የሊቃነ ጳጳሳት፤ ሱራፌል የጳጳሳት፤ ኀይላት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል፡፡በራማ ሰማይ የሚኖሩት አርባብ የቆሞሳት፤ መናብርት የቀሳውስት፤ ሥልጣናት የዲያቆናት አምሳል፡፡ በኤረር ሰማይ የሚኖሩት ሊቃናት የንፍቀ ዲያቆናት፤ መኳንንት የአናጒንስጢሳውያን፤መላእክት የመዘምራን አምሳል ናቸው፡፡

ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ “እንተ ተሐንጸት በስሙ፤ ወተቀደሰት በደሙ ወተዐትበት በዕፀ መስቀሉ ጊሡ ኀቤሃ እስመ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ” (በስሙ ታነጸች፤ በደሙምከበረች፤ በዕፀ መስቀሉም ተባረከች፤ ወደ ርሷ (ቤተ ክርስቲያንኺዱ የእግዚአብሔር ኀይል በርሷ ላይ ነውናይላል፡፡

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ተአምኆ ቅዱሳን በሚባለው ታላቅ መጽሐፉ ላይ፡- “ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እመ ኲሉ ሕዝብ፡፡ (የሕዝብ ኹሉእናት የመላእክት መዘዋወሪያ (ቦታየምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ይገባልብሏታል፡፡

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቤተ ክርስቲያንን “ቅድስት” አላት፤ ስለምን ቢሉየቅድስት ሥላሴ አንድነት ሦስትነት ይነገርባታልና፤

ጾም ማለት ምን ማለት ነው ? 

ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ ዝምድና አለው፡፡ ይልቁንም በብሉይ ኪዳን ጾምከፍተኛ ቦታ ነበረው፡
የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ ለአፋቸው አይገባም ነበር፡፡
/ዘዳ 34፥28/ በኃጢአታቸው ብዛት የመጣባቸው መዓት የሚመልሰው ቁጣውም የሚበረደው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር፡፡ /ዮና 3፥5-10/፡
በአዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይሆን ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕል ሥጋዌው መጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው፡፡ /ማቴ 4፥21/ ጌታችን በሦስት በፍቅረ ንዋይና በትዕቢት የሚመጣበትን ጠላት ዲያብሎስ በጾምድል እንድምንነሣው አሳየን፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር ጠላት ሰይጣንን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል /ማቴ 17፥21/፡
ስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሾሙትም በጾምና በጸሎት ነበር፡፡ /የሐዋ13፥3፤4፥25/ እነ ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ያላሰቡትን ክብር ያገኙት በጾማና በጸሎት ፈጣሪያቸው ማልደው ነው /የሐዋ 10፥20/
ጾም እንኳን የጠበቅነውንና ያሰብነውን ቀርቶ ያላሰብነውንና ያልጠበቅነውን ፈጽሞም የማይገባንን ጸጋና ክብር የሚያሰጥ ነው፡፡ ከሐዋርያት ቤተክርስቲያን በዓልና ትውፊት መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያዎቹአብያተ ክርስቲያናት አንዷ ስለሆነች የጾም ሕግና ሥርዓት አላት እነዚህም የፈቃድና የአዋጅ አጽዋማት ይባላሉ፡፡ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ የሐዋርያት (የሰኔ) ፆም ነው፡፡
ይህም ጾም በሕዝብ ዘንድ የወታደር ጾም ይባላል፡፡ ለስብከተ ወንጌል ዘመቻ የተዘጋጀ በጾሙት ተምሣሌት በድሮ ዘመን ወታደሮች ለዘመቻ ሲነሱ ወይም ከዘመቻ ሲመለሱ በተሳተ በተገጸፈ ይቅር በለን በማለት ይጾሙት ነበር፡፡ ይህምጾምየሚፈሰክበት ከሐምሌ 5 የማይለቅ ቢሆንም የሚጀመርበት ግን የተወሰነ ቀን የለውም በዚህም ምክንያት የጾሙ ዕለት ቁጥር ከፍና ዝቅ ይላል አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል አንዳንድ ጊዜ ከ30 ያንሣል የ2008 ዓ.ም. ጾም ሰኔ 13 ገብቶለሦስት ሳምንት ይጾማል፡፡
ሐዋርያት መቼ ጾሙ?
ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህሮቸዋል አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው /ሕሙማነ ሥጋን በተዓምህራት/ ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የሥራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊትእንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡
ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡ “እኛናፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎችሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ” /ማቴ 9፥15-16/፡፡
የሰኔ ጾም የቄስ ብቻ ነውን?
ይህ ጥያቄ ብዙ ሰዎች የሚነሣ ጥያቄ ነው ብዙ ምእመናን የሰኔን ጾም አይጾሙም ለመጾም የሚፈልጉትንም ሰዎች የቄስ ነው እያሉ ሲነቅፉ ይታያሉ ነገር ግን ይህ ጾም ከሰባቱ የአዋጅ ጾም አንዱ ነው፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌአድርገው የጾሙት እኛም እነርሱን አርአያ አድርገነው ልንጾመው የሚገባ የበረከት ጾም ነው፡፡ በዘመናችን ያሉ አንዳንድ “ክርስቲያኖች ነን” ባዮች “ከመጾም ተቆጥበው ቀሳውስት ብቻ የሚጾሙት ነው!” ይላሉ ለራስ የከበደን ነገር በሌላው ላይመጫን ተገቢ አይደለም ካላወቁ ለማወቅ መማር ዐውቆ ከማጥፍት መቆጠብ ተገቢ መሆኑን መዘንጋት አይገባም
እኛ ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመካፈል፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ዲያብሎስን ድል ማድረጊያ መሣሪያ አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ እንጂየቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምእመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡
እንዴትና ከምን እንጹም?
የጾም ሃይማኖታዊ ትርጉም ፈጣሪን መለመኛ ከኃጢአት ቁራኛ መላቀቂያ መሣሪያ ስለሆነ በጾም ወራት ለአምሮት ለቅንጦት የሚበሉ ወይም ለመንፈሳዊ ኃይል ተቃራኒ የሆኑ የአልኮል መጠጦች ሥጋና ቅቤ ወተትና እንቁላል ማራቅ ተገቢነው፡፡
ሥጋዊ ጉልበትን በጾም የማድከም ቅብአት ካላቸው ምግቦች መከልከልም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለው፡፡ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር “ጉልበቶቼበጾም ደከሙ ሥጋዮም ቅቤ በማጣት ከሳ” ብሏል /108፥24/፡፡ ሠለስቱ ደቂቅና ነቢዩዳንኤልም የቤተ መንግሥቱን ሥጋና የጸሎት ምግብ ትተው በጥሬና በውኃ መቆየታቸው ተጽፏል /ት.ዳን 1፥8-21፣ት.ዳን10፥2/ ዋናው ነገር ጾም እንጂ መብል ወደ እግዚአብሔር አያቀረበንም ብንበላም የምናተርፈው ባንበላም የሚጎዳን ነገርየለም፡፡ /1ኛ ቆሮ8 ፥8/ ከአዳም ጀምሮ መብል ሲጥል እንጂ ሲያነሣ አላየንምና ጾሙን ከኃጢአት በመራቅ ለራስ ያስብነውን ለነዳያን በመስጠት፣ ጾም ከጸሎት ጋር ሲሆን ጸጋን እንደ ሐዋርያቱ ያሠጣልና በጸሎት በመትጋት በስግደት ወደእግዚአብሔር በፍጹም ልብ በመመለስ ልንጾመው ይገባል፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም “ጾም የነፍስ ድግስ፣ ክብረ በዓል ነው” ብሎ ተናግሯል፡፡ ጾም ነፍስን ሐብታም ያደርጋታል፡፡ አዕምሮውን ንጹህ ከማድረጉም ባሻገር በጠላት ላይ መንፈሰ ጠንካራ ያደርጋል ጾም ጥሩ ሥነ-ምግባራትን የሚያዳብር መንፈሳዊሕይወት ነው፡፡ ይኸውም ንጽህናን፣ ትዕግስትን ድንግልናን፣ ደስታን ……ወዘተ በተጨማሪም የታላቁ ንጉሥ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተመቅደስ የሆነውን አካላትንን ለንጽህና ለእርሱ እንድናስገዛ ያደርገናል፡፡
ጾም ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ ያደርገናል፡፡ /ት.ኢዩ 2፥12/ “አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በለቅሶና በዋይታወደ እኔ ተመለሱ!” ወደ እግዚአብሔር የምንመለስበትን የልብ መነሳሳት እውነት ያደርግናልበጾማችን እግዚአብሔርን የምናደበት የቅድስና ሕይወት እንፈጥራለን ታላቁ ነቢዩ ኢሳይያስ በኃጢአቱ ተጸጽቶ የጾመው ጾም ለኃጢአቱ ሥርየት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርንም ክብር ለማየት አብቅቶታል /ት.ኢሳ6፥1/፡፡ በአጠቃላይ ጾምየመንፈሳዊ ሕይወታችን መሠረት ነው የአገልግሎትና የቅድስናችንም መጀመሪያ ሊሆን ይገባል፡

በእንተ ዐቢይ ጾም።

ዐቢይ ጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ካሏት ሰባት የአዋጅ አፅዋማት አንዱና ታላቁ በመባል የሚታወቀዉ ነዉ።
ታላቅ መባሉም በሁለት ዋና ጉዳዮች/ምክንያቶች ነው።

፩፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኃላ ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ በመሄድ ፵ ቀንና ፵ ሌሊት የፆመው ፆም በመሆኑ ነው።  እርሱ ለሐዲስ ኪዳን ፆም መሥራች በመሆኑ ነው። የምንፆመዉም እርሱን አብነት አድርገን እንድንፆም ያሥተማረበት፣መሰረት የጣለበት በመሆኑ ነው።
ማቴ፣ ፬ ፥ ፩ – ፩፪    ማር፣   ፩ ፥ ፩፪     ሉቃ፣    ፬ ፥ ፩ – ፩፫

፪፡  ከሌሎቹ ስድስት አፅዋማት በሚፆምበት የቀን ብዛት የሚበልጠው ይህ ጌታችን የፆመው ዐቢይ ፆም ነው።  ሁዳዴ ተብሎም ይጠራል።  ይህ ቃል ሰፊ የእርሻ ሜዳን/መሬትን የሚገልፅ ሲሆን ከሚፆምበት ቀን ጋር ተያይዞ የቀናቱን ብዛት ከሌሎች አፅዋማት ጋር በማነፃፀር የተሠጠው ስያሜ ነው።

ጌታችን የፆመው ፵ ቀንና ፵ ሌሊት ነው  እኛ ለምን ፶፭ ቀን እንፆማለን?

 

እንደ ቤተ ክርስትያን አሥተምህሮ ከ፵ ቀናት በተጨማሪ ያሉት ሁለት ሳምንታት አንዱ ከዘወረደ አስከ ቅድስት ያለዉና ፆመ ህርቃል ፣ ሁለተኛዉ ከሆሳህና እስከ ትንሳኤ ያለው ስሙነ ህማማት በቤተ ክርስትያናችን ሊቃውንት ከዋናው ፵ ፆም ጋር እንፆማቸዋለን።  ፆመ ህርቃል በመባል የተጨመረው አንድ ሳምንት ንጉስ የሀገሩን ክርስትያኖች ለመውረር የሚፈልጉትን አላዉያን ቢያስቸግሩት ወደ እግዚአብሔር ልመናውን በማቅረብ የመጡበትን ጠላቶቹን ድል ማድረግ በመቻሉ ከድል በኃላ አዋጅ አስነግሮ እንዲጨመር በማድረጉ የእግዚአብሔርን ረዳትነት በማስታወስ ማመስገን ይገባልና እኛም እንድንፆመው አድርገውታል።

ስሙነ ህማማት በመባል የሚታወቀው ከሆሳህና እስከ ትንሳኤ ያለው ጊዜ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያደረሱበትን ፍፁም መከራ በማሰብ ህመሙን የተቀበለውን መከራዎች የምናስበት ጊዜ እንዲሆን አድርገን የሚፆም ነው።  ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንእሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን በማለት እንደተፃፈው።  ሮሜ፣  ፮ ፥ ፭ – ፯

የዐቢይ ጾም ሳምንታት

 

በዐቢይ ጾም ዉስጥ ያሉ ሳምንታት በቁጥር ዘጠኝ ናቸው።  እስከ ትንሳኤ ያሉት እንደ ስያሜአቸው የየእለቱ ትምህርቶች ከሚመሳሰሉ  መልእክት ጋር አብለው ይዘረዘራሉ።
ከዚህ በታች እስከ ትንሳኤ ያሉትን መስበኮች እና መንባባት እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።

 

2345678910

 

 

One Comment:

  1. Appreciation to my father who told me about this
    web site, this blog is in fact remarkable.

    Here is my web-site … Ron Kadarishko

Comments are closed